There is strong need and demand to investigate and review the Harari regional state and the ruling HNL and OPDO parties for out off control corruptions and embezzlements of public funds and properties spanning twenty years. EPRDF is reluctant and oblivious to the crimes in Harari region. In the other way EPRDF is complicity and aiding and abetting the corruptions to destroy the foundations of the Harari society. As the result today Harar looks and feels rotten city inhospitable to its inhabitants. The question remains who dare review and investigate the bad and corrupt rulers of Harari regional state? If EPRDF couldn’t and wouldn’t do it who can? Injustice and corruptions rules Harar. Harar is calling and crying for justice and for the rule of laws and she knows no one is listening and caring.
Wednesday, 31 August 2011 09:30
By Tamiru Tsige
- በርካታ ባለሥልጣናትም እየታሰሩ ነው
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አፈ ጉባዔ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት አቶ ሀብታሙ ኢካ ፈለቀ፣ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከነሐሴ 20 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ መታሰራቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ አቶ ሀብታሙ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የክልሉ ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ያለመከሰስ መብታቸው ከተነሳ በኋላ ነው፡፡

-
ነሐሴ 20 ቀን 2003 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ያለመከሰስ መብታቸው ከተነሳ በኋላ በተጠረጠሩበት ወንጀል በፌዴራል ፖሊስ ተይዘው ወደ አዲስ አበባ የመጡት አቶ ሀብታሙ፣ የክልሉ አፈ ጉባዔ የሆኑት ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

አቶ ሀብታሙ በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በተለያየ ምርመራ ጉዳዩን ሲያጣራ ከርሞ፣ ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳለት ሳይጠይቅ እንዳልቀረ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥት በሚሰጠው ድጐማና የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለክልሉ ልማት በሚያደርጉት ዕርዳታ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ሳይጠፋ እንዳልቀረ ግምታቸውን የተናገሩት ምንጮች፣ ከአፈ ጉባዔው ጋር የተጠረጠሩ በርካታ ባለሥልጣናትና ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ሀብታሙ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉሕዴፓ) ሊቀመንበር መሆናቸውን ምንጮቹ ገልጸው፣ ከ1995 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2001 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሥራታቸው አስታውሰዋል፡፡

አቶ ሀብታሙና ሌሎች ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉበትን ምክንያት እንዲያብራሩልን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ መሐመድ ናስርን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት፤ ‹‹ከፍተኛ የግምገማ ስብሰባ ላይ ናቸው›› በሚል አልተሳካልንም፡፡ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ደውለን ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የፖሊስ አባል አቶ ሀብታሙ ኢካ ፈለቀና አንድ የክልሉ የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት እንደተነሳና መታሰራቸውን አረጋግጠው፣ ምርመራው ስላልተጠናቀቀ ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽንንም ጠይቀን በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ማግኘት አልተቻለም፡፡

No comments:
Post a Comment